# title: ጉማሬ ለመርዳት ሞከረ

ከተሸፈነው ጫካው ውስጥ ሆኖ ዝሆኑ ቴምቦ፣ አዳኙ በሳር እና በጥቂት እንጨቶች የሚሸፍነውን ጥልቅና ለመግደል የሚያስችል የጉድጓድ ወጥመድ ይመለከታል።

ቴምቦ “ሁሉንም እንስሳት ማስጠንቀቅ አለብኝ፣” ብሎ አሰበ ።

ቴምቦ ለእንስሳቶቹ ጫካቸው አደገኛ ቦታ እየሆነ መምጣቱን በጥብቅ አስረዳ። “ከወጥመድ ተጠንቀቁ!” ብሎ ቴምቦ ጮኾ ተናገረ።

ቴምቦ ወደ ወንዙ እየተቿኮለ ሄደ፣ በመንገድ ላይ ያገኛቸውን በሙሉ ኪቦኮ የሚባለውን ጉማሬን ጭምር አስጠነቀቀ፣ ። ለኪቦኮም “ዲክዲክን ካየኸው ከወጥመዱ እንዲጠነቀቅ ነገረው” አለው።